የኢትዮጵያውያን፡ ተራድኦ፡ ማህበር፡ በብሪታንያ፡ እ፡ኤ፡አ፡ በ1983 ፡ በአንጋፋነት፡ ተቋቁሞ፡ ላለፉት፡ 36፡ አመታት፡ በተለያዩ፡ ጊዜያት፡ በተለያዩ፡ ምክንያቶች፡ ከውድ፡ አገራቸው፡ በስደት፡ ለወጡ፡ በብዙ ሺህ፡ ለሚቆጠሩ፡ ኢትዮጵያውያን፡ ብሄር፡ ቋንቋ፡ ሀይማኖትን፡ ጾታ፡ ሳይለይ፡ ከፖለቲካ,፡ ነጻና፡ ገለልተኛ፡ በመሆን፡ የተለያዩ፡ አገልግሎቶችን፡ ማለትም፣ የስደተኝነት፡ ማመልከቻ፡ ድጋፍ፣ የመኖሪያ፡ ቤት፡ ፍለጋ፣ የጤና፡ የሴቶች፣ የህጻናትና፡ የአዛውንቶች፡ አገልግሎት፣ እንግሊዝኛ፡ቋንቋ፡ ትምህርት፣ የስራ፡ ፍለጋ፡ ስልጠናና፡ ምክር፣ የመሳሰሉትን፡ ማህበራዊ፡ አገልግሎቶችንና፡ ድጋፍ፡ በመስጠት፡ ላይ፡ ይገኛል።
የተራድኦ፡ ማህበሩ፡ የተቋቋመው፡ በእንግሊዝ፡ አገር፡ የግብረ፡ ሰናይ፡ ድርጅቶች፡ ህግና፡ ድንጋጌ፡ በመሆኑ፡ ከፖለቲካ፡ ነጻና፡ ገለልተኛ፡ ሆኖ፡ ለህብረተሰቡ፡ ተገቢውን፡ አገልግሎት፡ እየሰጠ የገኛል።
ተጨማሪ ይወቁእኛን በመደገፍ የሰዎችን ሕይወት አቅጣጫ ይቀይሩ! ከእርስዎ ጋር ለተገኙት ውጤቶች እናመሰግናለን።